በመተከል መንግስት ቀድሞ ካልተከላከለ ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡ ተሰማ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በመተከል መንግስት ቀድሞ ካልተከላከለ ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡን የጓንጓ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከክልሎቹ ከመንግስታት አስቸኳይ መልስ እንፈልጋለን ሲል አቤቱታውን አሰምቷል።

እያደረ የጥፋት መልኮች የሚቀያየሩበት መተከል ዞን በአዋሳኙ በሚገኙት የአማራ ክልል ወረዳዎች ጃዊ፣ጓንጓ ፣ዚገም እና ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ላይ ያንዣበበው ከፍተኛ ስጋት ንፁሃንን አጉል መሰዋትነት እያስከፈለ ሲሆን ይህ ቀጠና ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበት በመሆኑ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩ ግልፅ ነው።
ያለ ምክንያት እየተሰዋ ላለው ህዝባችን የሁለቱ ክልል መንግስታትና የፌዴራሉ መንግስት ዝምታ ባይገባንም አስቸኳይ የሰላም መፍትሔ የማይሰጥ ከሆነ ህዝባችን ላይ የሚደርሰው አደጋ የከፋ እንደሚሆን በተግባር እየተመለከትን በመሆኑ ከሶስቱ መንግስታት አስቸኳይ መልስ እንፈልጋለን።