በምዕራብ ትግራይ ያለው የፖለቲካ ሽኩቻ ለመልሶ ማቋቋም ስራዬ እክል ሆኖብኛል – የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከፌደራሉ መንግስትና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚመጡትን እርዳታዎች በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጂዎች ለማድረስ እየተሰራ ቢሆንም በምዕራብ በኩል በተለይም እንደ ሁመራና ዳንሻ ባሉ አካባቢዎች ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እንቅፋት እንደሆነበት አስተዳደሩ ገልፆል፡፡
በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋዊ እንደሚሉት በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
ይሁንና ይህ ሂደት ምሉዕ እንዳይሆን በምዕራብ ትግራይ ያለው የተፈናቃዮች ሁኔታ ባስ ሲልም የፖለቲካ ሽኩቻ ሲሉ የጠሩት ጉዳይ እንቅፋት እንደሆነ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ምዕራብ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ቢሆንም የኤርትራ ጦር ሰራዊት በስፍራው ስላለ ወደ ቀዬአቸው ላለመመለስ እንደ ምክንያት እያቀረቡት መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
አሐዱ ራድዮ 94.3