ከድሬዳዋ ወደ ደብረዘይት ሲበር የነበረ የመከላከያ ሰራዊት አውሮኘላን ተከሰከሰ።

የመከላከያ ሰራዊት አውሮኘላን ተከሰከሰ

በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ናናዋ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 4፡30 አካባቢ ከድሬዳዋ ወደ ደብረዘይት ሲበር የነበረ የመከላከያ ሰራዊት አውሮኘላን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ ሰዎች ህይወታቸው አልፈዋል፡፡

የአውሮፕላን የአደጋው ዝርዝር መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የኢፌዴሪ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግንኙነት መረጃ ያመለክታል።