ፖሊስ በደብረ ኤሊያስ ወረዳ ሰልፈኞች ላይ በከፈተው ተኩስ አንድ ሰው ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል።

በደብረ ኤሊያስ ወጣቶች እየታሰሩ ነው

በደብረ ኤልያስ ወረዳ ነሐሴ 6 ቤተክርስቲያን ሊያቃጥሉ መጡ በመባሉ ወጣቶች ያን ለመከላከል ሰልፍ አድርገዋል።

ፓሊስ ሰልፍ በወጣው ወጣት ተኩስ የከፈተ ሲሆን በተኩሱም የአንድ ወጣት ህይወት ሲያልፍ ሁለት ወጣቶች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።

ከዚህ እለት ጀምሮ እስካሁን ወጣቶች እየታሰሩ እና እየተደበደቡ ይገኛሉ። ከተደበደቡት እና ከታሰሩት መካከል ወጣት ተስፋየ የሽወንድ እና ባንታየው ዋሴ ይገኙበታል።

በትናንትናው እለት ብቻ 18 ወጣቶች ታስረዋል። ትእዛዙ የሚተላለፊው ምንያምር አባይነህ ከሚባለው የወረዳው አስተዳዳሪ ሲሆን አስፈፃሚወቹ የፓሊስ አዛዥ ሠለሞን እና ኢንስፔክተር ጌታነህ ናቸው ተብሏል።