የአማራ ብሄራዊ ንቄናቄ(አብን) ከአሜሪካ መንግስት ኮንግረስ አባላት ጋር ሊወያይ ነው፡፡

የአማራ ብሄራዊ ንቄናቄ(አብን) ከአሜሪካ መንግስት ኮንግረስ አባላት ጋር ሊወያይ ነው፡፡

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደገለጹት ነሃሴ 17/ 2010ዓ.ም የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ከአብን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ውይይት ያደርጋሉ፡፡

በውይይቱ የአፍሪካ ዓለማቀፍ ጤና ፣ሰባዊ መብት እና ዓለማቀፍ ተቋም ሊቀመንበር ክሪስ ስሚዝ እና በአሜሪካ የአብን ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ ይገኛሉ፡፡

የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ እንደነገሩን ከሆነ በውይይቱ ወቅታዊ የአማራ ፖለቲካና የኢትዮጵያ ሁኔታ፣አማራ ባለፉት ዓመታት ስለአሳለፋቸው የፖለቲካ ሂደቶች፣የኢትዮጵያ ዲሞክራሲና የፖለቲካ ስርዓቱ እንዴት ይሻሻላል እንዲሁም የአሜሪካ መንግስት የፖለቲካ ሂደቱን እንዴት ይደግፋል የሚሉ ነጥቦች በውይይቱ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡