በትግራይ የደፈጣ ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

 የመኪናው ረዳት ሁለት የፌዴራል ፖሊሶች ህይወት ሥድስት ተመራቂ ተማሪዎች

VOA : በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ ሥነ ሥርዓታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ የነበሩ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አዲመስኖ በምትባል አካባቢ በደረሰ የደፈጣ ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

በጥቃቱ ሥድስት ተመራቂ ተማሪዎች የመኪናው እረዳትና ሁለት የፌዴራል ፖሊሶች ህይወት ማለፉን ከጥቃቱ የተረፈ ተማሪ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ከአምስት ቀናት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡