ጌታቸው ረዳ በሞትና በህይወት መሀል የሚገኙ መንቀሳቀስ የማይችሉ ቁስለኞች የምትችሉ አምልጡ ብሎ የተሳለቀ ይሉኝታ ቢስ ከሀዲ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጌታቸው ረዳ በ”A” ደረጃ ተለይተው በሞት እና በህይወት መሀል የሚገኙ መንቀሳቀስ የማይችሉ ራሱ የላካቸው ቁስለኞች መሀል ከሙዚቀኞቹ አብርሃም ገ/መድህን እና አበበ አርአያ /የእንበር ተጋዳላይ ሞዛቂ/ ጋር ቆሞ ፣ የምትችሉ አምልጡ ብሎ የተሳለቀ ይሉኝታ ቢስ ከሀዲ ነው።

የካቲት 16 ቀን 2013

May be an image of 1 personበስተት እንኳን ከውሸት ውጭ እውነት ተንፍሶ የማያውቀው ጌታቸው ረዳ በትግራይ ምዕራባዊ ዞን መደባይ ዛና ወረዳ ውስጥ ፣ በመንገዱ ማብቂያ ሜዳ ላይ ፣ ስራችሁ ያውጣችሁ ብሎ ስለተዋቸው ራሱ ያዘመታቸው በርካታ ከባድ ቁስለኞች ግድ ሳይለው ፣ ቆላ ተንቤን ጉያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከድቷቸዋል ።

ከመቀሌ ጀምሮ ሲያጓጉዛቸው የነበሩትን አካል ጉዳተኛ የቀድሞ ታጋዮችን ከነቤተሰቦቻቸው ጥሎ የሸሸው ውሸታሙ ጌታቸው … ስለ ድል አድራጊነት ሲያወራ ከማዳመጥ በላይ ምን የሚደንቅ ነገር አለ?

እሱኮ በ”A” ደረጃ ተለይተው በሞት እና በህይወት መሀል የሚገኙ መንቀሳቀስ የማይችሉ ራሱ የላካቸው ቁስለኞች መሀል ከሙዚቀኞቹ አብርሃም ገ/መድህን እና አበበ አርአያ /የእንበር ተጋዳላይ ሞዛቂ/ ጋር ቆሞ ፣ የምትችሉ አምልጡ ብሎ የተሳለቀ ይሉኝታ ቢስ ከሀዲ ነው።

ከምላስ ውጭ የመሳሪያ ምላጭ ስቦ የማያውቀው ይሔ ሰው ፣ መከላከያ ሰራዊቱን እያረገፍነው ነው። ድል በድል ሆነናል ወዘተርፈ እያለ ሲቀባጥር ማዳመጥ በርግጥም አስቂኝ ነው።

ግን ደግሞ ውሾች ይጮሃሉ ግመሎቹም ከመሔድ አልቆሙም።

ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!!

ሻምበል ሰለሞን ሁነኛው ( ከግዳጅ ቀጣና )

FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት