በህዳሴ ግድብ ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ ሌላ አደራዳሪ አንፈልግም – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“በህዳሴ ግድብ ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ ሌላ አደራዳሪ አንፈልግም” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ላይ ከአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ አሜሪካ ፣ ተመድ እና የአውሮፓ ህብረትና በአደራዳሪነት እንዲሳተፉ ጥሪማቅረቧ ይታወሳል፡፡

ሱዳን ባለፈው ሳምንት ባወጣችው መግለጫ በሕዳሴ ግድብ ላይ ከአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ አሜሪካ ፣ የተባበሩት መንግስታት እና የአውሮፓ ህብረትና በአደራዳሪነት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርባ ነበር።

ይሁንና የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ “ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ ሌላ አደራዳሪ አንፈልግም” ብለዋል፡፡ ሌላ አደራዳሪ አንሻም ፤ የአፍሪካ ሕብረት ይዞታል ፤ ኮንጎ ነች ኃላፊነት የወሰደችው ሲሉ ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት።

ከድንበር ውዝግቡም ጋር በተያያዘ ሱዳን እንደ አውሮፓውያኑ ከህዳር 6 ጀምሮ ከያዘችው መሬት ለቃ ሳትወጣ ኢትዮጵያ ለድርድር እንደማትቀመጥ አምባሳደር ዲና በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ “ወደነበሩበት ከተመለሱ በደቂቃዎች ውስጥ ድርድር እንጀምራለን ብለናል” ነው ያሉት።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ