የትግራይ ሕዝብ በምግብ እህል እንኳን ራሱን ባልቻለበት ሁኔታ ሌላ የምግብ እርዳታ ተቀባይ እንዲሆን ያደረገ ሁኔታ የፈጠረው ወያኔ ነው – አቶ አንዳጋቸው ጽጌ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አቶ አንዳጋቸው ጽጌ ይናገራሉ…

👉 የትግራይ ሕዝብ በዋነኛነት ማወቅ ያለበት በክልሉ አሁን ያለውን ሁኔታ ያመጣው ጁንታው ሆን ብሎ ግጭት በመቀስቀስ የፈጠረው መሆኑን መገንዘብ ይገባዋል፤

👉 ሕግ የማስከበሩ እርምጃ አማራጭ የሌለው ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ተግባር ነው፤ በእርግጥም ከዚህ ውጪ ሌላ ሊደረግ የሚችል ነገር አልነበረም፤

👉 መንግሥት ሕጋዊ እርምጃውን ባይወስድ ኖሮ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን ያልተወጣ መንግሥት ይሆን ነበር፤

👉 የሕግ ማስከበሩ ዘመቻ በጣም ከፍተኛ ሆነ ውድመት ያስከትላል፤ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። ሀገሪቱን ወደ ባሰ ምስቅልቅል ይወስዳታል የሚል ስጋት ነበር፤
👉 በዋነኛነት የእኔን ስጋት ብዙ ሰዎች እንዲጋሩ ያደረገው በተከታታይ የወያኔ ባለሥልጣናት ጉልበታቸውን በመተማመን፤ በእጃቸው ያለውን የሰው ኃይልና ትጥቅ ማንም ሊገዳደር የማይችል ነው እያሉ በነዙት ወሬ ልክ መሆን አለመቻላቸው ነው፤
👉 በተጨባጭ እንደታየውም ያ ሁሉ ድንፋታና ፉከራ የራሳቸውንም አቅምም ሆነ የዘመኑን ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑ መንግሥት በቀላሉ መቆጣጠር የቻለበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው፤

👉 በቅርቡ እንኳን ጦርነት ለትግራይ ሕዝብ ባህላዊ ጨዋታው ነው ወደሚል እብሪት የገቡበት ሁኔታ ነበር። ያ ማንንም ማንበርከክ እንችላለን የሚለው ትርክታቸው ሦስት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፉከራቸው አፈር በበላበት ሁኔታ ነው የተዋረዱት፤

👉 በመጀመሪያ ደረጃ መታወቅ ያለበት ከሕግ ማስከበር ዘመቻ በፊትም ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የክልሉ ሕዝብ በሴፊቲኔት ሲረዳ የነበረው፤ በቀጥተኛ እርዳታ የሚኖረው ሕዝብ ቁጥርም ቀላል አልነበረም። ይሄ ከህግ ማስከበር ዘመቻው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤

👉 በእርግጥ በዚህ ደረጃ ከ27 ዓመታት የልማት ዘፈንና ፉከራ በኋላ የትግራይ ሕዝብ በችግር ላይ ወድቆ መገኘቱ አሳፋሪ ነው፤ ተጠያቂም የሚሆነው ያንን ክልል ሲመራ ነበረው የወያኔ ድርጅት ነው።

👉 የትግራይ ሕዝብ በምግብ እህል እንኳን ራሱን ባልቻለበት ሁኔታ ሌላ የምግብ እርዳታ ተቀባይ እንዲሆን ያደረገ ሁኔታ የፈጠረው ወያኔ ነው፤

👉 በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ባገኙት መገናኛ ብዙኃን ተጠቅመው የሚፅፉ ከ15 ያልበለጡ ሰዎች እንደሆኑ ነው እኔ የማውቀው፤ እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ በየትኛውም ድርጅትና ሕዝብ ዓይን ቦታ የሚሰጣቸው አይደሉም፤

👉 የትግራይ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በዚህ ሰዓት የሚፈልጉት ነገር ግልፅ ነው፤ የትግራይ ሕዝብ የመድኃኒትና የምግብ እርዳታ በአስቸኳይ ደርሶለት ከችግር እንዲወጣ ሳይሆን በሚሊዮኖች የሚያልቅበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው፤

👉 ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝባችንን አስጨረሰ የሚል የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት ነው፤

👉 ይህ አካሄዳቸው የተለመደና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለ የኢትዮጵያ ሊሂቃን የትግል አቅጣጫ ነው፤

👉 በእኔ በኩል መናገር የምፈልገው አንዱ ጉዳይ በተለያየ ምንጮች የሚመጡ ዜናዎችን መንግሥት ማጥራት አለበት ብዬ አምናለሁ፤

👉 መያዣ መጨበጫ የሌላቸው መረጃዎች እየወጡ ነው፤ ሁሉም ደግሞ ለራሱ ፍላጎት መሳኪያ ሲል እያጋነነ የሚያቀርባቸው ነገሮች እንዳሉ አውቃለሁ፤

👉 መደረግ ያለበትን ትክክለኛ ነገር በማድረግ ያንንም ጩኸትና የተጋነነ ወሬ እንዲሁም በሃሰት ላይ የተመሰረተ ክስ ከቁብ ሳይቆጥር ሙሉ ትኩረቱን የትግራይ ሕዝብ አሁን ካለበት ችግር ለማውጣት መስራት አለበት ብዬ አምናለሁ፤

👉 የነበረው የፖለቲካ ሥርዓት ይህንን ሕዝብና አገር በከፍተኛ ደረጃ የጎዳ በመሆኑ ይሄ ኃይል ከፖለቲካ መድረኩ መገለሉ በራሱ ትልቅ አገራዊ ፋይዳ አለው ብዬ አስባለሁ።


ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከስር ያለውን ሊንከ ተጭነው ያገኙታል።
https://www.press.et/Ama/?p=41670