የአድዋ ድል ለአፍሪካውያን የማንቂያ ደወል ነው – የደቡብ ሱዳን አምባሳደር


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


(ዋልታ) – የአድዋ ድል ለአፍሪካውያን የማንቂያ ደወል ነው ሲሉ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጄምስ ፒታ ሞርጋን ተናገሩ፡፡

የአድዋ ድል አፍሪካውያን በአንድ ላይ ሲሆኑ በሚፈጥሩት ጠንካራ ሕብረት ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ ማሳያ እንደሆነ ነው ከዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለፁት ፡፡

በኢትዮጵያውያን ድል የተነቃቁት አፍሪካውያን የራሳቸውን ነፃነት እውን ለማድረግ እንዲታገሉ ከማስቻሉ ባሻገር አፍሪካውያን በአንድ ላይ ሲሆኑ ሀይል እንዳላቸው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአድዋ ድልን በአንድ ቀን ካስመዘገበች አፍሪካውያን በአንድነት ችግሮቻችንን ህብረትና አንድነታችንን በማጠናከር የሌሎች አገራትን ጣልቃ ገብነትን አስወግደን የብልጽግና ማማ ላይ መድረስ እንችላለን ብለዋል፡፡

አምባሳደር ፒታ ሞርጋን የቅኝ ገዢዎች ያሰመሩትን የልዩነት ድንበር ማስወገድ እንደሚገባ ገልጸው፣ የአፍሪካን ህብረት ሰንደቅ አላማ አንዱን አገር ከአንዱ የሚለይ አንድም መስመር የለውም ይህም አንድነትን ያመላክታል ሲሉ አክለዋል፡፡

የአፍሪካን ህዳሴን እውን ለማድረግ በሰላም ግንባታ፣ በንግድ፣ በቱሪዝምና በኢንቨስትመንት ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር ለአፍሪካውያን ነጻ እንቅሳሴን መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

አፍሪካውያን የእርስ በእርስ ሽኩቻን ወደ ኋላ ትተን ለእድገት እና ለብልጽግና ኅብረታችንን በማጠናከር የአፍሪካን ትልቁ የልማት መሪ እቅድ የሆነውን አጀንዳ 2063 ማሳካት አለብን ብለዋል፡፡

አምባሳደር ጄምስ ፒታ ሞርጋን እንኳን ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ በማለት የድሉ ጀግኖች ያወረሱትን ማንነት አፍሪካውያን ድህነትን ድል በማድረግ መድገም እንዳለባቸው አስሳስበዋል፡፡