የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የነጻነት ቀን ብቻ ሳይሆን ለአፍካሪውያንም መነቃቂያ ነው – በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


(ዋልታ) – የአድዋ ኢትዮጵያውያን ነጻነታቸውን ያረጋገጡበት ቀን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካውያን ከቅኝ አገዛዝ ለመላቀቅ የሚያደርጉት ትግል ላይ መነቃቃትን የፈጠረ የድል በዓል ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሯ ከዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያውያን የዓድዋውን ጦርነት ያሸንፉት ከተለያዩ ቦታ የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን አንድንታቸውን እና ህብረታቸውን ሰላጠናከሩ መሆኑን ገልጸው፣ የዓድዋ ጦርነት የኢትዮጵያውያን የነጻነት ቀን ብቻ ሳይሆን ለአፍካሪካውያንም ነጻነታቻውን እንዲያረጋግጡ መነቃቂያ ሆኗል ብለዋል፡፡

አፍሪካውያን ከዚህ ድል አንድነት የሚያመጣውን ለውጥ መማር አለባቸው ያሉት አምባሳደሯ፣ እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ በመከባበር እና የጋራ ተጠቃሚነትን በመፍጠር አንድነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡

አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን ያለምንም ጣልቃ ገብነት በራሳቸው ለመፍታት ጠንካራ የሆነ መተሳሰብ እና መረዳዳት ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ወቅት ወደተለያዩ ሀገራት የመከላከያ ግብአቶችን በማጓጓዝ አፍሪካን አንድ ለማደረግ የተጫወተው ሰፊ ሚና የአፍሪካውያን ህብረት ከንግግር በዘለለ በተግባር የተደገፈ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የአድዋ ድል እና የኢትዮጵያና የቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 125 አመታቸውን ማክበራቸው የአድዋ በአልን እና ታሪካዊ ትስሰሩን ልዩ ያደርገዋል ሲሉ አምበሳደሯ ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ አገራት የመጀመሪያውን የመልእክት ልውውጥ ያደረጉት እ.ኤ.አ በ1869 በአጼ ምኒልክ እና በሱልጣን አብዱል ሀሚድ ሁለተኛ መካከል መሆኑ የታሪክ ድርሳናት ያመለክታሉ፡፡