ኢዜማ “ብርሃን” እንጂ “አምፖል ይዞ” ወደ ምርጫው አልመጣም – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢዜማ የምርጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት በኢዲስ አበባ ከተማ አከናውኗል።

የፓርቲው መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፓርቲያቸው “ብርሃን” እንጂ “አምፖል ይዞ” ወደ ምርጫው አልመጣም ሲሉ ተናገረዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፤ ገዢው ፓርቲ በምርጫ ምልክትነት የመረጠውን ቁስ ያነጻጸሩበት አገላለጽ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ የ“ይደገም” አድናቆት አስገኝቶላቸው ነበር።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ባሰሙት ንግግር፥ ገዢው ፓርቲ ከመጪው ምርጫ ጋር በተገናኘ “ግልጽ አቋሙን ሊያሳውቅባቸው ይገባል” ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል።

“ብልጽግና ፓርቲ የህወሓት እና የኢህአዴግ ወራሽ ሳይሆን ከሁለቱ የተለየ ፓርቲ መሆኑን በተግባር እንዲያሳየን እንሻለን” ብለዋል በንግግራቸው።

የኢዜማው መሪ፤ መጪው ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት አምስት ጠቅላላ ምርጫዎች የተለየ መሆኑን በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

“ኢህአዴግ ይባል የነበረው ድርጅት ስልጣን ከያዘ ወዲህ ምርጫ መሰል ነገሮች ሁሉ ተቆጥረው ስድስተኛ ይባል እንጂ፤ የእኛ ተስፋ ይህ ምርጫ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው” ሲሉ ለአሁኑ ምርጫ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት ተናግረዋል። “ታሪክ በእኛ ላይ የጣለው ሃላፊነት ይህ ምርጫ ከዚህ በፊት እንደነበሩት የይስሙላ ወይም የሙከራ ሳይሆን፤ በእርግጥም የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ ነው” ሲሉም አክለዋል።

ይህ ፁሁፍ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።