ኦነግ በምርጫዉ ሊሳተፍባቸዉ የሚችላቸዉ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዉበታል፣ ከምርጫው ወጥተናል – ዳዉድ ኢብሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጪዉ ግንቦት ሊደረግ በታቀደዉ ምርጫ መወዳደር እንደማይችል አስታወቀ።የግንባሩ ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ ዛሬ እንዳሉት ግንባራቸዉ በምርጫዉ ሊሳተፍባቸዉ የሚችላቸዉ መንገዶች በሙሉ ተዘግተዉበታል።አቶ ዳዉድ በተለይ ከዶቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በየአካባቢዉ የነበሩ የግንባሩ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተዋል፣ባለስልጣናቱና አባላቱ ታሥረዋል ብለዋል።ግንባሩ በምርጫዉ ለመወዳደር ከአምና ጀምሮ ሲዘጋጅ እንደነበረ አቶ ዳዉድ ገልፀዉ አሁን ግን ኦነግ በምርጫዉ እንዳይወዳደር «ተገፍቷል» ይላሉ-ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳ። DW