የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ የአማራነት ጉዳይ ፋይሉ የተዘጋ ነው – አቶ አገኘሁ ተሻገር

“የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ የአማራነት ጉዳይ ፋይሉ የተዘጋ ነው”
አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር
“በወቅቱ ሠዉ ለውጊያ ሳይሆን ለሠርግ የሚሄድ እድምተኛ ነበር የሚመስለው” የጠገዴ ወረዳ አስተዳደሪ ጌታቸው ሙሉጌታ
(አብመድ) ሁልጊዜም አሸናፊ፣ ሁልጊዜም ተዋጊ፣ ወንድነት ከእኛ በላይ ለሣር የሚለው ትህነግ በጀመረው እሳት ተለብልቦ ከዋሻ፣ ቤተመንግሥት ከቤተመንግሥት ወደ አንድ አካባቢ፣ ከአንድ አካባቢ ወደ ዋሻ ወርዶ ተበታትኗል። አብዛኛው ተይዟል፣ ሞቷል፣ የቀረውም እየታደነ መሆኑ እየተነገረ ነው።
እብሪተኛው ትህነግ የእብሪቱ የመጨረሻውን ሥራ ጥቅምት 24 አመሻሽ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ፈፀመ።በዚያም አላቆመም በአማራ ክልልም ጥቃት ፈፀመ። ዳግም የናፈቀውን ቤተመንግሥት አልሞ እሳት የለኮሰው ትህነግ በለኮሰው እሳት ተለብልቦ መድረሻው ጠፍቷል። የትህነግን ፍፃሜ ያበሰረችውን ቀን ጥቅምት 24ን የሚያስብ ዝግጅት በጠገዴ ወረዳ ተካሂዷል።
በዝክረ ጥቅም 24 በተደረገው ዝግጅት የጠገዴ ወረዳ አስተዳዳሪ ጌታቸው ሙሉጌታ ትህነግ ጦርነት አውጆ በወረዳው ለጦርነት ምቹ የሆኑ ቦታዎችን ለመያዝ ጥረት ቢያድርግም አስቀድሞ በደረሰው መረጃ መሠረት በአስደናቂ ጀብዱ ሳይሳካለት ቀርቷል ነው ያሉት። የጠላት ኃይል ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ ለመዋጋት ቢሞክርም በተደረገው ቆራጥ ትግል ማክሸፍ መቻሉንም አስታውሰዋል። “በወቅቱ ሠዉ ለውጊያ ሳይሆን ለሠርግ የሚሄድ እድምተኛ ነበር የሚመስለው” ነው ያሉት። በዚያ ውጊያ ታሪክ የሚያስታውሳቸው ጀብዱዎች መፈፀማቸውንም ተናግረዋል።
May be an image of 2 people and people standingትህነግ ሽፍቶችን በማደራጀት እና በማሰልጠን በወረዳው ወንጀል እንዲፈፀም ሲያድርግ እንደነበርም አስታውሰዋል። መንግሥት የትህነግን ሤራ በማዬት የተወሰደው ጥበባዊ እርምጃ የሚደነቅ እንደነበርም ተናግረዋል። ለትግራይ ሕዝብ ብዙ ነገር የሆነለትን የመከላከያ ሠራዊት ሲተነኩስ የአካባቢው ማኅበረሰብ በእልህ፣ ጥበባዊ በሆነ ወታደራዊ ጀግንነት በመነሳት እስከ አፍንጫው የታጠቀውን የጠላት ሠራዊት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ መልሶታልም ነው ያሉት።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ ወርቁ ኃይለ ማርያም በእብሪት የተከፈተብን ጦርነት በድል አጠናቀን በዋሻ ውስጥ የተደበቀው የትህነግ ኃይል በዳኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተዳኘበት ማግሥት መገናኜታችን እንኳን ደስ ያለን ብለዋል። ድል እንዲመጣ ተጋድሎ ላደረጉ ሁሉ ምሥጋና ይገባቸዋልም ነው ያሉት። ትህነግ አማራን ለማጥፋት ካልሆነም ለማሳነስ በሀሰት ትርክት በደል እንዲፈጸምበት ሲያደርግ እንደነበርም ተናግረዋል።
በትህነግ አገዛዝ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ግፍ ሲደርስበት እንደነበር ያነሱት አቶ ወርቁ ሕዝቡ ሲገደል፣ ሲፈናቀልና ሀብትና ንብረቱ ሲዘረፍ መቆዬቱንም አንስተዋል። በወልቃይት ጠገዴ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ከ10 ሺህ በላይ አማራዎች በግፍ መገደላቸውን እና ከ500 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንም ተናግረዋል።
May be an image of 8 people, people standing and outdoorsከሁለት ዓመታት በላይ ለጦርነት ሲዘጋጅ የነበረው ትህነግ በጥቅምት 24 ሀገራዊ ክህደት መፈፀሙንም አስታውሰዋል። ኢትዮጵያን የመካድ ልምድ ያለው ትህነግ በሶሮቃና በቅራቅር የፈፀመው ጥቃት በቁርጥ ቀን ልጆች ተደምስሷል ነው ያሉት። በዚህ ወቅት የትግራይ ሕዝብም ከትህነግ አገዛዝ ነፃ መውጣቱንም ተናግረዋል።
በግፍ የወሰዱብንን ታሪካችንን፣ የሠረቁትን ማንነታችንን በታሪክ መዝገብ አስፍረን እንፋረዳቸዋለንም ነው ያሉት። ትህነግ በፈጠራቸው አንዳንድ ኃይሎች የወልቃይት ጠገዴን ነፃ መውጣት ተራ የመሬት ማስመለስ አድርገው ይወስዱታልም ብለዋል። ከዚህ በኋላ መነሳት ያለበት በማን ይተዳደሩ የሚለው ሳይሆን ምን አይነት ፍትህ ይሰጥ? በደላቸውን እንዴት እንካሰው? እንዴትስ ይቋቋሙ የሚለውን በማንሳት ኢትዮጵያውያን ወደፊት ማራመድ ይገባልም ነው ያሉት። ፈጣን ምላሽ በመስጠት ከባለፈው ስህተት መማር ይገባልም ብለዋል።
ጥቅምት 24 ኢትዮጵያውያን ለማፍረስ የሚጥሩ አካላት ህልም ቅዠት የሆነበት መሆኑንም አስታውሰዋል። ውስጣዊ አንድነታችን በማጠናከር የሚገጥመንን ችግር እየፈታን ደጉን ሕዝብ መካስ ይገባልም ብለዋል።
May be an image of outdoors