በአራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ላይ ሲካሄድ የነበረው የወንጀል ምርመራ ተቋረጠ
***************
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙ አራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የወንጀል ምርመራ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡
–
ምርመራቸው እንዲቋረጥ እና ከእስር እንዲለቀቁ የተደረጉት የጦር መኮንኖች፦
1. ሜ/ጀ መሀመድ ኢሻ ዘይኑ ትኩእ
2. ብ/ጀ ሙሉጌታ በርሄ ይልማ
3. ኮ/ል ገ/እግዚአብሔር ገ/ሚካኤል እና
4. ኮ/ል ገ/ዋህድ ኃይሉ መሸሻ ናቸው፡፡
–
በጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩት መኮንኖቹ የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ክትትል ተይዘው ለምርመራ ቡድኑ ተላልፈው የተሰጡ መሆናቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
–
በዚሁ መሠረት ተጠርጣሪዎቹ ፈጸሙ በተባሉበት ወንጀል ምርመራ ሲካሄድባቸው የቆዩ ቢሆኑም የምርመራ ቡድኑ ባደረገው ማጣራት የወንጀል ተሳትፎአቸው ዝቅተኛ መሆኑን በመገንዘብ ምርመራው ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ መደረጉን ቢሮው በተለይ ለኢቲቪ ገልጿል፡፡
–