በስሜት መነዳትና የፖለቲካ ጥላቻ ወደ ገደል ሳይከተን መቆም አለበት ።

በስሜት መነዳትና የፖለቲካ ጥላቻ ወደ ገደል ሳይከተን መቆም አለበት ። ምንሊክ ሳልሳዊ

ለተለያዩ ጊዜያት በፖለቲካ ጥላቻ የተሞላ መናቆርና መፈራረጅ እርስ በርስ መናከስ እንዲቆም ጮኸናል። ይህ የዘር ፖለቲካ ያመጣብንን ፍዳ ልንቋቋመው የምንችለው ተባብረን ተራርመን ተመካክረን ተከባብረን በኢትዮጵያዊነት ስንቆም ነው ካልሆነ የሚደርስብን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ኪሳራ ሰብዓዊ ቀውስ ያሸክመናል።

ከፖለቲካው ጥላቻ በተጨማሪ በጭፍንና በስሜት መነዳት ሌላው ነገ ላይ አደጋን የደቀነ እኩይነት ነው። ካለፈ መማር ያልቻልን የራሳችም ጠላቶች መሆናችንን አቁመን የጋራ ሃገራዊ ራእይ መያዝ ይጠበቅብናል። በተደጋጋሚ እንደሚባለው በወሬና በጭብጨባ አገር አይመራም። ጭቆናን የተሸከመ ሕዝብ ነጻነት መሸከም እንዳይችል አድርገው ወደ ስርዓት አልበኝነት የሚወስዱ በስሜት የሚነዱ ፖለቲከኞች ሊቆነጠጡ ይገባል።

ለለውጥ የሚደረገውን ትግል ማሳካት የምንችለው ይዘነው የመጣነውንን ትግል አጠናክረን ስንቀጥል ብቻና ብቻ ነው። ለውጡ አመጣጡና ምንጩ ከየትም ይሁን ለውጥ የምንፈልግ ሃይሎች ግን ያገኘነውን መስመርና እድል ተጠቅመን የሕዝብን ነጻነትና መብት በተግባር እንዲተረጎም የማድረግ ግዴታ አለብን። የማይሆኑ ፕሮፓጋንዳዎችን በመንዛት ሕዝብ ያገኘውን የነጻነት ተስፋ እንዲያጣ የምናደርገውን መታከክ ልናቆም ይገባል። #MinilikSalsawi


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE