በማንነት እና በብሔር የመቧደን እንቅስቃሴ የመቀየር አላማ ግሎባል አሊያንስ እንዳላቸው አርቲስት ታማኝ በየነ ተናገረ

ግሎባል አሊያንስ ከሌሎች የሰብዓዊ መብት ማኅበራትና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመሆን ለትግራይና ለመተከል ተጎጂዎች እርዳታ ለማሰባሰብ የሚያደርገው ርብርብ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተለመደ የመጣውን የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት በማንነት እና በብሔር የመቧደን እንቅስቃሴ የመቀየር አላማ እንዳለው የድርጅቱ ዴሬክተር አርቲስት ታማኝ በየነ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር በቀላሉ በእርዳታ ብቻ እንደማይፈታ የሚናገሩት ታማኝ በየነ፤ እርዳታ ማሰባሰቡ ቢያንስ አንደኛው አንደኛውን“አለሁልህ” የሚል ስሜት መፍጠሪያ ነው ያለ ሲሆን፣ ይህ ሐሳባቸው ተቀባይነት አግኝቶ ፤ሰዎች ከአንድ የታሸገፓስታ ጀምሮ ያላቸውን በማዋጣት ላይ መሆናቸውንም ገልጿል።

/ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።/