ተደብቆ ከተገኘው ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ዘይት ጀርባ ያለው ባለሃብት ማን ነው ?

በአዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ
በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ነው፡፡EBC
ተደብቆ ከተገኘው አንድ መርከብ ጀሪካን ዘይት ጀርባ ያለው ባለሃብት ማን ነው ? – ዋሲሁን ተስፋዬ
………
No photo description available.አሁን ገበያ ላይ ባለው ዋጋ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ጀሞ አንበሳ ጋራዥ አጠገብ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን በዜና ሰምተናል ።
ህዝብ በዘይት እጦት ሲማረር ይህን የሚያህል ጀሪካን ደብቆ የተገኘው ባለሃብት ስም ፖሊስ ለምን ይፋ አያደርግም ? በርግጥ ይህን ያህል ሃብት በፖሊስ ሊያዝበት እንደሆነ ያወቀው ሰው ፖሊስን በመደለያ ለመያዝና ጉዳዩን ለማፈን ጥረት ሳያደርግ የሚቀር አይመስለኝም ፡ ሆኖም ፖሊስ በዚህ ሳይደለል ይህን በቢሊየን የሚቆጠር ህገወጥ ክምችት መያዙ ግዴታውም ቢሆን መመስገንም አለበት ። ሆኖም ግን ከመያዙ ዜና በተጨማሪ ፡ ባለቤትነቱ የእንትና በሆነው እንደዚህ የሚባል ድርጅት የተቀመጠ ዘይት ነው ብሎ ለምንድነው የማይነግረን ?
No photo description available.የሚሊየን ሰወች ችግር ምንም ሳይመስለው ፡ አንዳንድ ጀሪካን ዘይት ቢገዛ እንኳን ሁለት ሚሊየን ህዝብ ሊጠቀምበት የሚችልን ነገር ፡ በመጋዘን አሽጎ እስኪወደድ ጠብቆ ለመሸጥ የሞከረን ስግብግብ ነጋዴ ሰብአዊ ክብሩ እንዳይነካ ነው ? ወይስ በየቦታው በቅለው እንደተገኙት ባለቤት አልባ ህንፃዎች ዘይቱም ባለቤት የለውም ?
መሸፋፈን ይብቃ ፡ የዚህ ሰው ማንነት ሊያውቅ ህዝብ ይፈልጋል ። በቀጣይ በዚህ ባለሃብት ቢዝነሶች ላይ 🚫 ማእቀብ በማድረግ በእጦቱ ሲቀልድ ለነበረው ለዚህ ስግብግብ ባለሃብት የህዝብን ፓወር ማሳየት ያስፈልጋል ።
በዚህ ደሃ ህዝብ ገንዘብ በተሰራ መንገድ ላይ የሚነዱት የስምንትና የአስር ሚሊየን ብሮች መኪና የተገኘው ፡ ከዚህ በእጦት ሊቀጡት ከሚፈልጉት ህዝብ ከሚገኝ ገንዘብ መሆኑን እነሱ ካልገባቸው ፡ ህዝቡ እንዲገባቸው ሊያደርግ ይገባል ። ዋሲሁን ተስፋዬ
No photo description available.