የጥምቀት በዓል በዓለም ላይ በእምነታችን የምንታወቅበት ታላቅ በዓል ነው – ብጹዕ አቡነ ማቲያስ

የጥምቀት በዓል በዓለም ላይ በእምነታችን የምንታወቅበት ታላቅ በዓል ነው – ብጹዕ አቡነ ማቲያስ
Image may contain: 1 person, on stage and beard(ኢዜአ) “የጥምቀት በዓል በዓለም ላይ በእምነታችን የምንታወቅበት ታላቅ በዓል ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ገለጹ።
የከተራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብሯል።
በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በተከበረው የከተራ በዓል ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ብጹዕ አቡነ ማቲያስ “ይህ በዓል ዓለም ዓቀፍ በዓል ሆኗል” ሲሉ ባለፈው ዓመት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን አስታውሰዋል።
የጥምቀት በዓል በዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ በርካታ ቱሪስቶች የሚታደሙበት እንደሆነ ገልጸዋል።