ጎጃም ሸበል በረንታ ውስጥ በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመ ት/ቤት ስያሜው ተቀየረ።

በአማራ ልጆች ትግል ለመለስ ዜናዊ መታሰቢያነት የተሰየመው ትምህርት ቤቶች ስም ወደነበረበት እየተቀየረ ነው! ( አቻምየለህ ታምሩ )

መለስ ዜናዊ ያለውን አቅምና ጉልበት ሁሉ ሳይቆጥብ ለክፉ ተግባር ያዋለ፤ በእምነትና በቅን መንፈስ ተገፋፍቶ ያለፋቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙበት፤ በትምህርት ተወልደው መልካም የሚሰሩና ለወገናቸው የሚያስቡ ሰዎችን በማጥፋት ክብረወሰን የተቀዳጀው፤ ድሀ ዘራፊና ገፋፊ፤ ተራ ወንጀለኛና ጨካኝ አረመኔ ነበር።

እኛ የምናውቀው መለስ ዜናዊ በካድሬዎቹ እንደሚወራለት ማለፉ ዓለምን ያጎደለ፣ አፍሪካንም ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ ያሳጣና ሞቱ አህጉሩንም የጎዳ ሳይሆን ተሰርቶ ያላለቀና ከፈረንጅ አፍ ሰምቶ በማስታወሻ ደብተሩ የያዘውን ሁሉ በአንድ አዳር የአገር ፖሊሲ በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ብክነት ማዕከልነት ሲቀይር የኖረ በጥላቻ የናወዙ የትግራይ አረመኔያዊ ሽፍቶች አለቃ ነበር። የገነባው የአፓርታይድ አገዛዝ እስኪያንገሸግሸን ድረስ የመተረን ተጠቃን ብለን የማንጮህ፤ ተዘረፍን ብለን የማንቆጣ፤ ሕጋዊ ስርዓት ተፋለሰ ብለን የማንበሳጭ፤ የድሃውና የስራ አጡ ለቅሶ ሰሚ ሳይኖረው የጭቆና አስተዳደር ተከናንበን የምንኖር ህዝቦች በመሆናችን፤ ኩራትና ክብራችን ዋጋ አጥቶ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ታፍኖ እያየን በልቶ በማደር የኑሮ ግዴታ ብቻ ስለተጠመድን ብቻ ነው።

በጭካኔ ክብረ ወሰን የሰበረው መለስ ዜናዊ ምልክቶች ከኢትዮጵያ ምድር ተነቅለው መወገድ ይኖርባቸዋል። ለሱ ሐውልት ማቆም የሚሻ ቢኖር ከመለስ ዜናዊ ጋር በጭካኔ የሚመትሩት አገር ለመመስረት ጫካ የገቡት እነ ኦነግ፣ ኢሕአፓ፣ ሻዕብያ፣ ጀብሃ፣ መኢሶን፣ ወዘተ ጋር ተባብሮ ቢፈልግ ደደቢት በረሀ፣ አሊያም አሲምባ ተራራ፣ ቢያሻቸው ሞቃዲሾ ዚያድ ባሬ ቤተ መንግሥት ወይንም ናቅፋ ተራራ ላይ በእጁ መዶሻና አካፋ፤ በትክሻው ደግሞ የቻይናና ሩሲያን ባለ ቢጫ ኮከብ ቀይ ባንዲራ አስይዞ ሐውልት ያቁምለት።

በቀናት በፊት በየአካባቢው ፋሽስት ወያኔ ወያኔ በግንቦት ፳፣ በመለስ ዜናዊና በትግራይ ነጻ አውጪዎች ስም የሰየማቸው ወይንም የቀየራቸው የሕዝብ መገልገያዎች እየታደኑ ወደ ነባር ስማቸው እንዲቀየሩ የተጠናከረ ዘመቻ መከፈት ይኖርበታል ብለን ነበር 🙂 በዚህም መሰረት በየአካባቢው ፋሽስት ወያኔ በግንቦት ፳፣ በመለስ ዜናዊና በወያኔ ነጻ አውጪዎች ስም የሚጠሩ የትምህርት ቤትና የሌሎች የመገልገያ ስሞች እየታደኑ ሕዝብ በመረጠው መጠሪያና ወደ ቀድሞ ስማቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በዛሬው እለትም ጎጃም ሸበል በረንታ ውስጥ በክፋት መምህሩ በመለስ ዜናዊ ስም «የሸበል መለስ ራዕይ አጠ/ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት» በሚል ይታወቅ የነበረው የሕዝብ ትምህርት ቤት በአማራ ልጆች ተጋድሎ ሕዝብ በመረጠው ስም « ሸበል አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት በም/ቤት» ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል።

አሁንም በየአካባቢው ፋሽስት ወያኔ በግንቦት ፳፣ በመለስ ዜናዊና በሌሎች የትግራይ ነጻ አውጪዎች ስም የቀየሩ ወይንም የተጠሩ የቦታና የመገልገያ ስሞች እየታደኑ ወደ ቀድሞ ስማቸውና እንዲቀየሩ የተጠናከረ ተጨማሪ ዘመቻ መከፈት ይኖርበታል!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE