የተባረሩ መምህራን በጊብሰን አካደሚ አንጻር ያሰሙት ወቀሳ

በአዲስ አበባ የሚገኝ ጊብሰን አካዳሚ የተባለ የግል ትምህርት ቤት መምህራን አላግባብ ከስራ መባረራቸውን  ተናገሩ። ከተለያዩ የትምህርት ቤቱ  ቅርንጫፎች የተባረሩት አስር መምህራን የትምህርት ስርዓት ጥራት እንዲጠበቅ እና የሰራተኞችም መብት እንዲከበር መጠየቃቸው ለመባረራቸው ምክንያት እንደሆነ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።…