ስደተኞችን የሚረዳ የኢትዮጵያውያን ማህበር በኑርንበርግ 

ወደ ሥራው ከመግባታቸው በፊት በጀርመን ህግ መሠረት አስፈላጊ የሆነውን ሥልጠና መውሰዳቸውን የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ አህመድ ሲራጅ ይናገራሉ። አቶ አህመድ እንዳሉት ይህን ስልጠና መውሰዳቸው በአካባቢያቸው በሚገኝ ትልቁ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በኤድስ ላይ ያተኮረ የምክር አገልግሎት መስጠት አስችሏቸዋል። …