ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ከፈለገች ወታደሮቿን ማስወጣት አለባት – በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

  • ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያሰራጨውን ዘርዘር ያለ መረጃ
  • ክቡር አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ልዩነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አሳሰቡ

ካርቱም (ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም.):የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ድንበር ኮሚሽን እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 13 ቀን 2021 ተቀማጭነታቸው በሱዳን ለሆኑ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች፣ ቆንስላዎች እና የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ባዘጋጁት የገለጻ መድረክ ላይ በሱዳን የኢ.ፌ.ድ.ሪ አምባሳደር ክቡር ይበልጣል አዕምሮ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ ባሉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እና የጋራ የድንበር መድረኮች አማካኝነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለባቸው አሳሰቡ።

በዚህ ረገድ አምባሳደሩ ከዳግልሽ ተራራ በስተሰሜን ከሰፈራ እና ከእርሻ መሬት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲመጣ የሚደነግገው እና በሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እ.ኤ.አ. በጁላይ 18 ቀን 1972 የተደረገው የማስታወሻ ልውውጥ ከፍ ያለ ፋይዳ ያለው እንደሆነ በአጽንኦት አስረድተዋል።

አያይዘውም በ1972ቱ የማስታወሻ ልውውጥ በተቀመጠው መሰረት የጉዊን መስመርን ዳግም ማካለል ከመጀመሩ በፊት ከዳግልሽ ተራራ በስተሰሜን ከእርሻ መሬት እና ሰፈራ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ልዩ ኮሚቴው ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ ያካተተ ሪፖርት ለጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ማቅረብ እንደሚኖርበት ገልጸዋል።

ምንም እንኳ የጋራ ልዩ ኮሚቴው ሁለቱን ሀገሮች የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ ለማቅረብ ስምንት ዙር ስብሰባዎችን ቢያካሂድም ኃላፊነቱን ገና እንዳላጠናቀቀ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር የጋራ ልዩ ኮሚቴ ስራ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጥቅምት ወር መጨረሻ ህግ ለማስከበር ወደ ትግራይ ክልል ያደረገውን ስምሪት እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀሙን እንስተዋል።

በዚህ መሰረት የሱዳን ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት ንብረት ከመዝረፉ፣ ወታደራዊ እና የእርሻ ካምፖችን ከማቃጠሉ ባሻገር በኢትዮጵያውያን ላይ እስራት፣ ጥቃት እና ግድያ መፈጸሙ እንዲሁም በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀሉን ጠቅሰዋል። ይኸውም የ1972 የማስታወሻ ልውውጥን በግልጽ የጣሰ ተግባር መሆኑን አስረድተዋል።

አምባሳደሩ አክለውም በሁለቱ እህትማማች ሀገራት ጸንቶ ከቆየው አጋርነት እና ትብብር መንፈስ በተቃረነ መልኩ አጋጣሚውን በመጠቀም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ለቋቸው የወጣ ካምፖችን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።አምባሳደሩ በተጨማሪም ሱዳን በችግር ውስጥ በነበረችበት ጊዜ ሁሉ ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ ጎን መቆሟን አውስተው፣ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ በተጠመደችበት ወቅት ከሱዳን ሰራዊት የደረሰባት ጥቃት የሚገባት እንዳልነበረ ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በገለጻቸው አክለውም የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት ካልተወሰደ፣ ታይቶ የማይታወቀው የሱዳን ሰራዊት ተግባር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ብሎም የጋራ ድንበሩን ዳግም የማካለሉን ስራ የሚያወሳስብ እና ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች እንዲሁም ለቀጠናው ከፍ ያለ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚኖረው መሆኑን አንስተዋል።በመጨረሻም ክቡር አምባሳደሩ የኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ልዩነቱን ሁለቱ ሀገራት በገቧቸው ስምምነቶች እና ባሉ የጋራ የድንበር መድረኮች መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ለችግሩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት፡

አንደኛ፣ የሱዳን ሰራዊት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፈጸመውን ወረራ በመቀልበስ በ1972ቱ የማስታወሻ ልውውጥ በተቀመጠው መሰረት ወደ ቅድመ-ኖቬምበር 2020 (እ.ኤ.አ.) እንዲመለስ፣

ሁለተኛ፣ ወደ ድንበር ዳግም ማካለል ከመገባቱ በፊት የጋራ ልዩ ኮሚቴው በ1972 የማስታወሻ ልውውጥ መሰረት ከዳግሊሽ ተራራ በስተሰሜን ከሰፈራ እና እርሻ መሬት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱን ሀገራት የሚያስማማ የመፍትሔ ሃሳብ የማቅረብ ስራውን እንዲያጠናቅቅ፣

ሶስተኛ፣ የጋራ ድንበሩን ዳግም ለማካለል ሁለቱ ሀገራት ያቋቋሟቸው የጋራ የድንበር ኮሚሽን፣ የጋራ የቴክኒክ የድንበር ኮሚቴ፣ እና የጋራ ልዩ ኮሚቴ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እና ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያሰራጨውን ዘርዘር ያለ መረጃ

H.E Ambassador Yibeltal Aemero Underscores the Need for Peaceful Resolution of the Differences Regarding the Ethio- Sudan Boundary

===========================================

Khartoum ( 13 January 20212): At a briefing session organized by the Sudanese Ministry of Foreign Affairs and National Borders Commission on 13 January 2021 for diplomatic missions, consulates and international organizations accredited to Sudan, H.E Yibeltal Aemero, Ambassador Extraordinary Plenipotentiary of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to the Republic of the Sudan,underscores the need for Ethiopia and Sudan to resolve their differences on the boundary peacefully as per the bilateral agreements and joint boundary mechanisms put in place to handle the matter.

In this regard,the Ambassador particularly emphasized the significance of the exchange of notes made between the Foreign Ministers of the two countries on 18 July 1972 that provides for amicable solution to the problem arising from settlement and cultivation North of Mount Dagelish.He further stated that,as per the 1972 Exchange of Notes, prior to the re-demarcation of the Gwynn line North of Mount Dagleish, the Joint Special Committee should submit to the Joint Ministerial Commission a report containing an amicable solution to the problem arising from settlement and cultivation.

Although,the Ambassador indicated,the Joint Special Committee convened 8 rounds of meetings to carry out the task of proposing an amicable solution, it has not yet finalized its mandate.

Ambassador Yibeltal Aemero further stated that while the work of the Joint Special Committee was still in progress and when the Ethiopian National Defence Forces moved to the Tigray region on November 4, 2020 for law enforcement operation, the Sudanese Army taking advantage of the internal situation in Ethiopia entered inside Ethiopian territory and looted property,burned civilian camps,killed and attacked Ethiopians while displacing thousands in flagrant violation of the 1972 Exchange of Notes.Besides, the Ambassador added,contrary to the spirit of friendship and cooperation existing between the two sisterly countries, the Sudanese Army took and controlled vacated Ethiopian Military Camps.

The Ambassador also underlined that, Ethiopia which has been on the side of the Sudanese people during all times of difficulties, does not deserve such an attack from Sudanese Army while it was busy of managing its own internal affairs.

Ambassador Yibeltal in his briefing also mentioned that all the recent unprecedented action of the Sudanese Army will complicate the bilateral relations including the pending task of the re-demarcation of the common boundary with huge implications to peoples of the two countries and the region at large unless corrected urgently.

He finally underscores Ethiopia’s firm commitment to peacefully resolve the boundary issue between Ethiopia and Sudan on the basis of the bilateral agreements reached and the joint boundary mechanisms put in place to handle the matter.

The Ambassador further indicated Ethiopia’s view on the way forward as follows:

First, the recent intrusion by the Sudanese Army needs to be reversed and the pre-November 2020 status quo should be maintained as per the 1972 Exchange of Notes.

Second, the Joint Special Committee needs to finalize the task of proposing an amicable solution as per the 1972 Exchange of Notes to the problems arising from settlement and cultivation North of Mount Dagleish which is a prerequisite for the re-demarcation of the Gwynn Line North of Mount Dagleish.

Third, the joint boundary mechanisms put in place for the re-demarcation of the boundary (Joint Boundary Commission, Joint Technical Boundary Committee and the Joint Special Committee) need to be reactivated to discharge their mandates.