የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል የተባሉት እነግርማ ካሳን ጨምሮ ለ11 የፖሊስ አመራሮች ዋስትና ተፈቀደ

ፍርድ ቤቱ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ ለ11 የፖሊስ አመራሮች ዋስትና ፈቀደ

በአዲስ አበባ ሰኔ 16 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ላስመዘገቧቸው ለውጦች በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በሚል ምርምራ እየተካሄደባቸው የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ዋስትና ተፈቀደላቸው።

አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።

የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል።

ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ገብረስላሴ ታፈረ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄና ኮማንደር አንተነህ ዘላለምን ጨምሮ ሌሎች የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው የነበሩ ግለሰቦች ከ6 ሺህ ብር እስከ 9 ሺህ ብር በሚደርስ ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል።

በዚህም የዋስትና ጉዳይን የሚመለከተው መዝገብ መዘጋቱን ነው ፍርድ ቤቱ ያስታወቀው።

FBC


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE