በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በነበረው ውጥረት እና በሱዳን ባለው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሐገራቸው ተመለሱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

ከ3,500 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ተመለሱ።

ከ3500 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ወደኢትዮጵያ መግባታቸውን የመተማ ዮሐንስ አካባቢ የመንግስት ኃላፊዎች እና የኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማስታወቁን ናሁ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የመተማ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ባለሞያ የሆኑት አቶ ስጦታው ጫኔ ፥ ኢትዮጵያውያኑ ሱዳን ውስጥ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ሱዳን (ገዳሪፍ አካባቢ) በግብርና እና በቀን ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ብለዋል።

ከ80% በላይ የሚሆኑት ከካርቱም ነው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት።

ከሰሞኑ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በነበረው ውጥረት እና በሱዳን ባለው የኢኮኖሚ ቀውስ ኢትዮጵያውያኑ መመለሳቸውን ገልፀል።

አሁንም ከሱዳን ወደኢትዮጵያ የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የኮሚኒኬሽን ባለሞያው ጠቁመዋል።

ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ የሱዳን ጦር ምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች የፈፀመውን ትንኮሳ የከትሎ አካባቢው ውጥረት ስፍኖበት መቆየቱን ቴሌቪዥን ጣቢያው በዘገባው አስታውሷል።