«የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም» ጠበቆች

ፍርድ ቤት የሚለቃቸውን ተከሳሾች ፖሊስ አለመልቀቁ እንዳማረራቸው ጠበቆች አመለከቱ። ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ  ማግስት በወንጀል ተጠርጥረው ታስረው ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ከውጭ እንዲከታተሉ የዋስትና መብታቸውን የጠበቀላቸው ቢኖሩም ትዕዛዙ እየተከበረ እንዳልሆነ ጠበቆቹ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። …