የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተማርከዋል፤ የተደመሰሱም አሉ – ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው

በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቻውን እና መደምሰሳቸውን የመከላከያ ሐይል ሥምሪት መምሪያ ሐላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አረጋግጠዋል።
በውጭ የሚገኙ የጁንታው ሚዲያዎች የሐሰት ኘሮፓጋንዳ ቢያናፍሱም ፣ የመከላከያ ሐይልና ፌዴራል ፓሊስ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ ፣ በርካቶች ተማርከዋል ። እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትም ተደምስሰዋል ብለዋል።
የተቀሩትም በየእምነት ተቋማትና ገዳማት ፣ ዋሻና ሸለቆዎች እራሳቸውን ደብቀው እንደሚገኙ መረጃ እንዳላቸው የገለፁት ጄኔራሉ ፣ ጁንታው የሞቱበትን ከፍተኛ አመራሮቹን ከሰብአዊ ርህረሄ ውጭ በሆነ መልኩ እንዳይታወቁ አንገታቸውን ቆርጦ ለየብቻ ስለሚቀብራቸው ለመለየት አዳጋች መሆኑን ተናግረዋል።
የጁንታ ሐይል ተደምስሷል ። በየሸለቆው የደበቃቸው የህዝብና የመንግስት ንብረት ተይዟል ያሉት ሐላፊው ፣ ጁንታው በህይወት እንዳለ በአንዳንድ አካላት ከውጭ የሚነዛው ኘሮፖጋንዳ ፍፁም ሐሳት መሆኑን አስረድተዋል።