የ«ኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት»ፕሮጀክቶችና የዘጌ ገዳም ተጠቃሚዎቹ 

ድርጅቱ በአካባቢው በመሰረታቸው ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች ከመኖሪያቸው ሳይርቁ መማር መቻላቸውን እንዲሁም እናቶች በየቤታቸው ውሀ በአቅራቢያቸው ማግኘት መቻላቸውን መስክረዋል። ድርጅቱ እንደሚለው ከ35 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተለያዩ ተቋማትን አስገንብቷል። የባሕር ዳር አስተዳደር ድርጅቱ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ሥራ ማከናወኑን አረጋግጧል።…