የሶማሌ ክልል ልዩ ሐይል በምስራቅ ሐረርጌ 32 ሰወችን ገደለ።

የሶማሌ ልዩ ሃይል ምስራቅ ሃረርጌ ማዩ ሙሉቄ ወረዳ ሮጌ ቀበሌን በመውረር የ32 ንፁሃን ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል።

ልዩ ሃይሉ አገር ሰላም ብለው ኑሮአቸውን እየገፉ በነበሩት ዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀሙት በእለተ እሁድ ጧት 4 ሰዓት አከባቢ ጀምረው እስከ 10:00 ሰዓት ሲሆን ዛሬ ከተገደሉት ውስጥ 19ኙ ነዋሪዎች ሲሆኑ 13ቱ የኦሮምያ ፖሊስ መሆናቸው ተዘግቧል።