ጅቡቲያውያን ኢትዮጵያውያን የግድያና ከሃገር የማባረር ዘመቻ ጀምረዋል ፤ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል።

ጅቡቲያውያን ኢትዮጵያውያን የግድያና ከሃገር የማባረር ዘመቻ ጀምረዋል ፤ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል።

የኢትዮ ኤርትራን ስምምነት ተከትሎ ጥቅማችን ቀረ ብለው የተበሳጩት ጅቡቲያውያን በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የተነሳውን ቀውስ በድሬዳዋ የተገደሉትን ጅቡታውያን ተንተርሰው ኢትዮጵያውያን ላይ የግድያና ከሃገር የማባረር ዘመቻ ባለፉት ሶስት ቀናት ጀምረዋል። የዓይን እማኞች እንደሚናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ የበቀል እርምጃ ወስደዋል። ምሽትን ተገን በማድረግ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማቁሰላቸውና ስድስቱን መግደላቸው የታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያውያን ንብረት የሆኑ ሱቆችን ማውደማቸው ሲታወቅ ፖሊስ እያየ ዝም ማለቱን እማኞቹ ይናገራሉ።

 

በድሬዳዋ ነዋሪ የሆኑ ጅቡቲያውያን ሲገደሉ እንደፈነዳ የሚነገርለት ይህ ዓመጽ መነሳቱን ተከትሎ በርካቶች በተለይ የኦሮሞ ተወላጆች ኢትዮጵያውን መፈናቀላቸው ንብረታቸው መዘረፉና መቃጠሉ ሲታወቅ ተጎድተዋል ተገድለዋል። ጅቡቲ ወደ ሁለት ሺህ ዜጎቿን ከድሬዳዋ አስወጥታለች። በሶማሌ ክልል የርእሰመስተዳደሩን ከስልጣን መባረር ተከትሎ በድሬዳዋ የሚኖሩ ደጋፊዎቻቸው መጤ ባሏቸው ሕዝቦች ላይ ግድያ ፈጽመዋል። #Miniliksalsawi