በችሎት ያልተገኙት እነጀዋር መሀመድ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆነ

እነጀዋር መሀመድ በአቅራቢያችን ችሎት ጉዳያችን ይታይልን ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆነ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገመንግስትና የፀረ ሽብር ወንጀሎች ጉዳይ ችሎት የእነ ጀዋር መሀመድን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል፡፡
ከዚህ በፊት አቶ ጀዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሀ ባቀረቡት የጽሁፍ አቤቱታ ለደህንነታችን ስለምንሰጋ ችሎቱ በአቅራቢያችን ይሁንልን ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
ይህንን የመረመረው ችሎቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ በዚሁ ችሎት ጉዳያቸው እንዲታይ አዝዟል፡፡
ለጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ዛሬ አራቱ ተጠርጣሪዎች በችሎቱ ያልተገኙ ሲሆን በመዝገባቸው ስር የተካተቱ ቀሪዎቹ ግን ተገኝተዋል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው።