የሱዳን ባለሀብቶች ትህነግን አስከትለው ወደ ኢትዮጵያ ከ40 ኪሎ ሜትር በላይ ገብተዋል

የሱዳን ባለሀብቶች ትህነግን አስከትለው የአማራ ገበሬን ሀብትና ንብረት ሲያቃጥሉ፣ ሲዘርፉ ነው የሰነበቱት። የደረሰውን የገበሬ ማሽላ እየቆረጡ ወደሱዳን ሲወስዱ ነው የሰነበቱት። ወደ ኢትዮጵያ ከ40 ኪሎ ሜትር በላይ ገብተዋል።
ዛሬ በረከት በተባለ አካባቢ ነው የአማራ ልዩኃይልና ሚሊሻ እነዚህን ባለሀብት የላካቸው ኃይሎች እንዲመለሱ ያደረገው። በሌሎች አካባቢዎች ግን ከ50 በላይ ባለሀብት እርሻዎችን ይዘዋል። የትህነግ ሰዎች ያሉበት መሆኑን በግልፅ የሚያሳየው ደግሞ የአማራ እርሻ ካምፖችን ለይተው ሲያቃጥሉ መሰንበታቸው ነው!
መንግስት ከሱዳን መንግስት ጋር በሚኖረው ውይይት መረጃዎችን በሚገባ ሰብስቦ ይነጋገር። አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ግልፅ ነው። የውጭ ሀገር ሚዲያዎችም ጉዳዩን ትኩረት ሰጥተው ሊያጋግሉት ይችላሉ።
መንግስት መረጃዎችን በደንብ ይዞ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋርም ይወያይበት፣ ለሚዲያዎችና ለሌሎችም ለማስረዳት አካባቢው ላይ ምን እንደተፈጠረ በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። – Getachew Shiferaw