የኢትዮ ሶማሌ ክልል አስተዳደር የሕዝብ ተቋም ሳይሆን የማፊያ ድርጅት እንደሆነ ተገለጸ።

መታየት ያለበት ቃለ-መጠይቅ!

ኢቲቪ ዛሬም እንደትላንቱ ሁለት የክልሉ ምሁራን ጀባ ብሎናል-አደም ፋራህና መስጠፋ ኡመር! ሙስጠፋ ኡመር ከዓመት በፊት ለምን ስለኔና ስለክልሉ ትፅፋለህ በማለት አራጁ አብዲ ኢሌ ታናሽ ወንድሙን ኢንጂኔር ፌይሰልን ከመኪና ላይ በመወርወር ገድሎበታል፡፡ ሙስጠፋም በአብዲ ኢሌ ካገራቸው ካሰደዳቸው ምሁራን መካከል ይገኝበታል፡፡አደም ፋራህም የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከአብዲ ኢሌ ጋር ባለመስማማታቸው ስልጣናቸውን ሊለቁ በቅተዋል፡፡

እነዝህ ሁለት ምሁራን የክልሉ ችግር አስተዳደራዊ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡ ሰብአዊ መብት ጥሰት፣ አምባገነናዊነት በክልሉ ተባብሶ ይታይ እንደነበረ ይገልፃሉ፡፡ መግደል፣ ማፈናቀል፣ ግጭት መፍጠር ከሌላው በተለየ ሁኔታ የክልሉ አይነተኛ መለያ ባህሪ እንደነበረም አውስተዋል፡፡
ምን መደረግ አለበት? ለሚለው ሁለቱ ምሁራን የሚከተለውን ሀሳብ አቅርበዋል::
• ሕግና ሥርዓት ማስከበር፤
• የተዘረፉ ንብረቶች ማስመለስ
• ወንጀል የፈፀሙትን ተጠያቂ ማድረግና ለህግ ማቅረብ፡፡ ለተጎጂዎች የፍትህ ሥራ መስራት!
• የልማትና የዲሞክራሲ ችግሮችን መቅረፍ ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እነዝህን የክልሉን ምሁራን በማማከር ክልሉ ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት የሱማሌን ሕዝብ መካስ ይኖርበታል፡፡ እስከአሁን ድረስ አብዲ ኢሌን የመሰለ አራጅና መሀይም ሕዝቡ ላይ በመጫን ለመናገር የሚከብድ በደል በሕዝብ ላይ ተፈፅሟል፡፡ ካለፈው ትምህርት ወስደን ለሚመሰረተው መንግስት የሱማሌ ሕዝብ ምርጫ እንድከበር እንጠይቃለን!