ጠሚ አብይ አባይ ሚዲያ ያሉት የተዘጋውን በደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆኑት አቶ ሐጎስ ኃይሉ የተመዘገበውን”አባይ ኤፍ ኤም 102.9″ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት የተዘጋውን የ”አባይ ኤፍ ኤም 102.9″ የሚባለውን የተዘጋ ሬዲዬ ጣቢያ ነው።

“አባይ ኤፍ ኤም 102.9” ጣቢያና ኢ ኤን ኤን ቲቪ (ENN TV ) ባለቤታቸው ተመሳሳይ ነበር። የደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን እ.ኤ.አ በጁን 2014 በደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ ካለምንም ፎርማሊቲና መስፈርት አባይ ኤፍ ኤም ለተባለው የራዲዮ ጣቢያ ፈቃድ እንዲሰጠው ተደርጓል። በወቅቱ እንደ ባለስልጣኑ መግለጫ ለአዲስ አበባ ከተወዳደሩት መካከል መስፈርቱን አሟልቶ የተገኘው አባይ ኤፍኤም 102.9 ሬዲዮ ጣቢያ ሲፈቀድለት ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ተሰርዘዋል፡፡#MinilikSalsawi

የአባይ 102.9 ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት የደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆኑት አቶ ሐጎስ ኃይሉ ነበሩ።