ሕወሓቶች ስለሕገመንግስት የማውራት ሞራል የላቸውም ፤ ሕወሓትን በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም እንቀጣዋለን።

ሕገመንግሥት ይከበር ያሉ ዜጎችን በአሸባሪነት ሲያስሩና ሲያሳድዱ የነበሩ ሰወች ስለሕገመንግስት የማውራት ሞራል የላቸውም ። ሕወሓትን በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም እንቀጣዋለን።(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ትላንት በተለያየ መንገድ ሕገመንግስቱ እንዲከበር የጠየቁ ዜጎች ላይ አረመኔያዊ ተግባር የፈጸሙ ያስፈፀሙና የደገፋ ዛሬ የመርሕ ሰው ሆነው ስለሕገመንግስት አፋቸውን ሞልተው መናገር ይፈልጋሉ። ዛሬ ሕገ መንግስት ይከበር የማለት ሞራሉን ከየት አመጡት ? ከ25 አመት በላይ ሐገሪቷ ፍትሕ አልባ ስትሆን የሚሰቀጥጡ ወንጀሎች እና መንግስታዊ ሽብሮች ሲፈፀሙ እዚሁ አብረውን ነበሩ ፤ እኛ ስንጮህ ራሳቸው ያወጡትን ሕግ እንዲያከብሩ ስንጠይቅ አሸባሪ ብለው ሲፈርጁን ነበር።

አንድም ቀን ስለሕገመንግስትና ስለመንግስታዊ ሽብር ተንፍሰው አያውቁም ። ከባባድና አደገኛ የሕግ ጥሰቶችን ዝም ብለው እያየዩ ጥቅማቸው ሲነካ ስለሕገመንግስት ቢያወሩ የሚሰማቸው የለም። ከአደባባይ ግድያ እስከ ኢሰብአዊ ስቃይ ሲፈፀም ፣ በክልሎች ጣልቃ ገብነት ጀምሮ እስከ አደገኛ አፈናዎች ሲፈፀሙ ፣ የሕግ የበላይነት ሲደፈጠጥ ወዘተ ዛሬ ላይ ሕገ መንግስት ይከበር የሚሉ ሰወች ሕገመንግስቱን ሲጥሱ ሲያስጥሱና ገዳዮችን ሲደግፉ የነበሩ ጥቅመኞች ናቸው ።ትላንት ስላልቆሙለት ሕገመንግሥት ዛሬ ላይ ለማውራት ምንም ሞራል የላቸውም።

ዜጎች በተለይ በአገር ውስጥ ያሉ ከሰላማዊ ሰልፍ ጀምረው እስከበይነ መረብ ዘመቻ ለሕገመንግስቱ ክብር እንዲሠጥ ጮኸዋል ። በምላሹ ከመንግስት የተሰጣቸው ዱላ እስር እና ስደት ነበር ፤ ዛሬ ላይ አሳሪዎች ገዳዮች ገራፊዎች ዘራፊዎችና ወዳጆቻቸው ለእኩይ አላማቸው ስለ ሕገ መንግስቱ ጠበቃ ሆነው ቆመዋል። እፍረት ያልፈጠረባቸው እነዚህ ድኩማኖችና የቀን ጅቦች በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም እንቀጣቸዋለን ። #MinilikSalsawi