ትግራይ ፡ በማይካድራ ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ

በማይካድራ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ቢያንስ 600 ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥሩም ከዚህ እንደሚበልጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። ኮሚሽኑ ይህንን የገለጸው በማይካድራ ከተማ የተከሰተውን ጥቃት ተከትሎ በከተማዋና በአካባቢው ባሉ ሌሎች ስፍራዎች ያካሄደውን ምርመራ ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ ነው።…