አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር የዋለው በአንቀፅ 39 መሰረት የሶማሌ ክልልን ለመገንጠል ስብሰባ በመጥራቱ እንደሆነ ታወቀ!!!

መከላከያ ገብቶ ከተማውን ተቆጣጥሮታል። መከላከያ በኦራል እየዞረ ከተማውን እያረጋጋ ነው። የሚዘርፉትን ዘርፈዋል ሄደዋል። እንቅስቃሴ የለም። ሕዝብ በየቤቱ ተቀምጧል በሶማሌ ክልል ጎዴ ቀብሪደሀር፣ ደገሀቡር፣ የመሳሰሉ ከተሞች ውስጥ ውጥረት ነግሷል፡፡ ከሶማሌ ውጪ ባሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች ላይም ጥቃት እየተሰነዘረ ነው፡፡

Abdi Illey will be placed under federal custody “in order to prevent further bloodshed in the region. (addis Standard)

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር የዋለው በአንቀፅ 39 መሰረት የሶማሌ ክልልን ለመገንጠል ስብሰባ በመጥራቱ እንደሆነ ታወቀ!!!

የሱማሌ ክልል ፕረዜዳንት አብዲ ኢሌ በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑ እርግጥ ነው። በትላንትናው ዕለት አብዲ ኢሌ ከፌደራሉ መንግስት እና የፀጥታና ደህንነት ኃላፊዎች ጋር በክልሉ እየተባባሰ ስላለው የፀጥታ ችግር ለመነጋገር ስብሰባ ተጠርቶ ነበር። አብዲ ኢሌ ግን ከፌደራሉ መንግስት የቀረበለትን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው የክልሉን ፓርላማ እና ካቢኔ ስብሰባ ይጠራል። የዚህ ስብሰባ ዋና ዓላማ የሕገ-መንግስቱን አንቀፅ 39 በመጠቀም የሱማሌ ክልልን ለመገንጠል ውሳኔ ለማሳለፍ እንደሆነ ታውቋል። በዚህ መሰረት ዛሬ ጠዋት አብዲ ኢሌ ከክልሉን ምክር ቤት እና ካቢኔ አባላት ጋር ስብሰባ ላይ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥጥር ስር ውሏል። ከሰዓት በኋላ በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርቦ የክልሉ ሕዝብ እንዲረጋጋ ጥሪ አቅርቧል። ማታ ላይ ደግሞ ስለ ጉዳዩ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ይሆናል። ሆኖም ግን አብዲ ኢሌ አንቀፅ 39 መሰረት የሲማሌ ክልልን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ጥረት ማድረጉ የተረጋገጠ ሀቅ ነው። ፍፁም ባልተጠበቀ መልኩ ሀገር ለመገንጠል ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት ግን በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል። በቀጣይ ምን ሊሆን እንደሚችል አብረን የምናየው ይሆናል። ለበለጠ ማብራሪያ ይህን የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ መመልከት ይቻላል።

https://addisstandard.com/breaking-federal-defense-forces-surround-somali-regional-state-president-abdi-mohomud-omar-situation-remains-tense/


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE