በሰኔ 16 ቦንብ ፍንዳታ የመሩት ተክላይ በላይ ፀሃዬ እና ግርማይ ከበደ ለመያዝ ፖሊስ ፍለጋውን ቀጥሏል።

ተክላይበላይ ፀሃዬ እና ግርማይ ከበደ የሚባሉ ሁለት ሰዎች ከቦምብ ፍንዳታው 1ቀን ቀደም ብለው የተሰወሩና እስካሁንም ዱካቸወን ያጠፉ ሲሆን የምርመራ ግብረሃይሉም እያሳደዳቸው እንደሆነ ታውቅዋል።

የሰኔ 16ቱ ፍንዳታ በሶስት የምርመራ ምድቦች እና በአራት የምርመራ መዝገቦች ነዉ እየታየ ያለዉ።

ሁለቱ የምርመራ ምድቦች፥

1ኛ. ሃላፊነታቸዉ ላይ ክፍተት በመፍጠር የተጠረጠሩ ሲሆኑ

2ኛ. ድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ የተጠረጠሩ ናቸው።

በመጀመሪያዉ የምርመራ ምድብ ስር (ሃላፊነትን ባለመወጣት) የአዲስአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ግርማ ካሳን ጨምሮ 10 የፌደራል እና የአዲስአበባ ፖሊስ ሃላፊዎችን እና አባላትን ይዞ የተከፈተ የምርመራ መዝገብ ሲሆን አሁን ምርመራዉን ለማጠናቀቅ የመጨረሻዉ ቀጠሮ ላይ ይገኛል።

በሁለተኛዉ ምድብ ስር (በቀጥተኛ ተሳትፎ) የተከፈቱት ሶስት የምርመራ መዝገቦች ሲሆኑ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡

የመጀመሪያዉ፡ የምርመራ መዝገብ (የነ አብዲሳ ቀነኒ) ዛሬ ምርመራዉ መጠናቀቁ የተገለፀዉ እና አምስት ተጠርጣሪዎችን የያዘዉ ሲሆን ሁሉም የፍንዳታው እለት ቦታዉ ላይ በህዝብ ትብብር በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸዉ።

በሁለተኛዉ መዝገብ ስር ሁለት ተጠርጣሪዎች የሚገኙ ሲሆን ለሽብር ተግባሩ የሎጀስቲክ ድጋፍ በማድረግ የተጠረጠሩ ናቸዉ።

በሶስተኛዉ የምርመራ መዝገብ ስር ያሉት ትላልቆቹ ናቸዉ። በረጅም እጃቸው እሳት ወደ ህዝብ የላኩትን የሚመለከት ሲሆን በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የፀረ-ሽብር ግብረሃይል ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ ሌሎች እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የደህንነትና መከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩ ግለሰቦች ይገኙበታል።

ተክላይበላይ ፀሃዬ እና ግርማይ ከበደ የሚባሉ ሁለት ሰዎች ከቦምብ ፍንዳታው 1ቀን ቀደም ብለው የተሰወሩና እስካሁንም ዱካቸወን ያጠፉ ሲሆን የምርመራ ግብረሃይሉም እያሳደዳቸው እንደሆነ ታውቅዋል።

ምርመራዉ ሰፊና ዉስብስብ በመሆኑ እና እስካሁን ያልተያዙትን እነዚህን ተጠርጣሪ የደህንነትና የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት ለመያዝ የምርመራ ቡድኑ ከትላንት ወዲያ ፍ/ቤቱን ተጨማሪ ቀን ጠይቆ ረዘም ያለ ቀጠሮም ተፈቅዶለታል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE