የመከላከያ ሠራዊት በወሳኝ የሕወሕት ዒላማዎች ላይ ከመቀሌ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት አካሂዷል – ግብረ ኃይሉ

በሁለት ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት፣ በመቐለ የአየር ጥቃት መደረጉን የሚገልጹ አርዕስት እና አጭር ቪዲዮዎች ወጥቷል። እነዚህ መረጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይሉ ሳያረጋግጡ በሕወሐት መረጃ ላይ ብቻ የተመሠረቱ ሐሰተኞች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሂደቱ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚለው መረጃም እንዲሁ ሐሰት ነው፡፡
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ በወሳኝ የሕወሕት ዒላማዎች ላይ ከመቀሌ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን የማስከበር እንቅስቃሴ ዒላማን በጥንቃቄ መምታትን መሠረት ያደረገ ነው። ሕወሐት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃቱን ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት ሲል ከከተሞች የራቀ ጥቃት ላይ አተኩሯል:: – Ethiopia State of Emergency Fact Check
Image