ኢትዮጵያ በጅቡቲ እና ኤርትራ መካከል ያለውን አለመግባባት ልትሸመግል ነው

በጅቡቲ እና ኤርትራ መካከል ያለውን አለመግባባት ኢትዮጵያ ልትሸመግል ነው

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንደተናገሩት ሁለቱ አገራት የኢትዮጵያ ወዳጆች በመሆናቸው ለመሸምገል ፍላጎቱ እንዳላት አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የሽምግልና ጥያቄ ለጅቡቲ አቅርባ ተቀባይነት ማግኘቱንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ኤርትራና ኢትዮጵያ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት ከፈቱ በኋላ በምስራቅ አፍሪካ ያለው የሰላም ፍላጎት እያደገ መጥቷል ተብሏል፡፡

በሌላ ዜና በውጭ አገራት ኢትዮጵያን ወክለው እንዲሰሩ የተሾሙ አምባሳደሮች በነገው ዕለት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙም አቶ መለስ አለም ቃለ መሃላ ተናግረዋል፡፡

በነገው ዕለት ቃለ መሃላ የሚፈፅሙትና የሙሉ አምባሳደነት ሹመት ያገኙት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ አቶ እሸቱ ደሴ፣ አቶ አዛናው ታደሰ፣ አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣ አቶ ድሪባ ኩማ፣ አቶ ያለው አባተ እና አቶ አብዱልፈታ አብዱላሂ ናቸው።