በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ5 መቶ በላይ የሚገመት ህገ ወጥ የክላሽ ኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል የስራ ሂደት መሪ ኢንስፔክተር መሃመድ አህመድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት ሁለት ቀን በፊት ከጉባ ወደ አሶሳ በሚመጣ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ዉስጥ በሁለት የልብስ ሻንጣ የተሞላ 5 መቶ የክላሽንኮቭ ጥይት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ህብረተሰቡ በሰጠዉ ጥቆማ በሆሞሻ የፍተሻ ኬላ ላይ ጥይቶቹ ከአዘዋዋሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከባለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ከ37 በላይ የሚሆኑ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ መሃመድ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለዉ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ሪፖርተር፡ ያለለት ወንድዬ (አሶሳ)