ስግብግቡ የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በክልል ከተሞች ተካሔዱ

ጅማዎች በሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመን ጥቃት በማውገዝና መንግስ መቀሌ በመሸገው ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻውን በመደገፍ በዝህ መልኩ ሰልፍ ወተዋል።

ከሃዲውን የህወሃት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአጋሮ ከተማ እየተካሄደ ነው ከሃዲውን የህወሃት ቡደን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በጅማ ዞን አጋሮ ከተማ መካሄድ መጀመሩን ከጅማ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Image may contain: 12 people, crowd

ጂጂጋ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ቁጣ እና ቁጭት በሰልፍ ተገለጠ

ወንበዴው እና ስግብግቡ የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ሰልፉ በተካሄደበት የጅግጅጋ ስታድየም ባደረጉት ንግግር፣ ስግብግቡ ጁንታ አፀያፊ ተግባር በሶማሌ ሕዝብ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያሳረፈው ቁስል ሳይሽር በቅርቡ የሀገር አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ተግባርም እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
የሰልፉ ዓላማም ወንበዴው የሕውሓት ቡድን በሥልጣን ዘመኑ ያደረሰውን ግፍ እንዲሁም ከሰሞኑ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን ጥቃት እና አሁንም እያደረገ ያለውን የክህደት ተግባር ለማውገዝ መሆኑን አቶ ሙሰጠፌ አስታውቀዋ። ተጠያቂነት የማይሰማው ይህ ወንበዴ ቡድን በዘር፣ በሃይማኖት እና በብሔር እያደረገ ያለውን የመከፋፈል ሥራም እንደሚያወግዙት ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ የተናገሩት።
ስግብግቡ የሕወሓት ቡድን ለ27 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ከባድ በደል አድርሷል ያሉት የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች፣ በቅርቡ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመውን አስነዋሪ ጥቃት አውግዘዋል።
ይህ ቡድን የፈፀመው ተግባር አስነዋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ድርጊቱ ችግሮችን በሰላም እና በውይይት ይፈታል የሚለውን ተስፋቸውን ያሟጠጠ እንደሆነም ገልጸዋል። የመከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለውን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚደግፋ የገለጹት ተሳታፊዎቹ፣ የእናት ጡት ነካሽ የሆኑትን የቡድኑን አባላት ለሕግ የማቅረብ ሥራም ያለምንም ድርድር ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጠይቀዋል።ቡድኑ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የፈፀመው ዓይነት ተግባሩን ማስቆም የሚቻለው የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ብቻ እንደሆነም እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል። የዚህ ቡድን አባላት በመላው ኢትዮጵያዊ ላይ ከፍተኛ በደል ማድረሳቸውን፣ በተለይ ደግሞ በሶማሌ ክልል በሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከልም መከፋፈል እንዲመጣ ሲሠሩ መቆየታቸውንም ተናግረዋል።
ከሃዲው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የወሰደውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው። በሰላማዊ ሰልፉ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። ሰልፈኞቹ ከሃዲው የህወሃት ጁንታ ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት መፈክሮችን በመያዝ እያወገዙ ነው።
ከመፈክሮቻቸው መካከልም ”በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ከሃዲው ጂንታ የህወሃት ቡድን የወሰደውን እርምጃ እንቃወማለን፤ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ሆነን የሚጠበቅብንን ድጋፍ ሁሉ እናደርለን” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል። ሰልፈኞቹ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን አጋርነትም በመግለጽ ላይ ናቸው።
ምንጭ፤ ኢዜአ