ባሻን ሰዓት እየተመላለስን ለህግ እስኪቀርብ ማጥቃታችንን እንቀጥላለን – የአየር ሀይል አዛዥ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

አየር ኃይላችን ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን የኢፌዴሪ አየር ሀይል አስታወቀ።

Image may contain: 1 personኢትዮ ኤፍ ኤም – የኢፌዴሪ አየር ሀይል የህወሃት ቡድንንን ለማንበርከክ ባሻው ሰዓት ተመላልሶ መደብደቡን እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ይልማ ዛሬ እየሰጡት ባለው መግለጫ እንዳሉት አየር ኃይላችን ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ምርጥ ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ገልጸዋል።

ለጁንታው እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ኢላማዎችን ጀቶቻችን ያለምንም ከልካይ እንዳሻቸው እየተመላለሱ አውድመዋቸዋልም ብለዋል።

ፓይለቶቻችን የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ እንደሚገኙም አስረድተዋል ።

ጁንታው እንመታለን የሚለው ፣ እድሜውን ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ባህሪው ነው ያሉት ሜ/ጀ ይልማ ፣ ባሻን ሰዓት እየተመላለስን ለህግ እስኪቀርብ ማጥቃታችንን እንቀጥላለን ብለዋል ። – ኢትዮ ኤፍ ኤም