በጃዊ ወረዳ -ፈንድቃ ከተማ በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጃዊ ወረዳ -ፈንድቃ ከተማ በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሀምሌ 24/2010 በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳ -ፈንድቃ ከተማ በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ።

ኃላፊው እንደገለፁት በጣና በለስ የስኳር ፕሮጀክት ይሰሩ በነበሩ ዜጎች ህይወት ላይ ትላንት ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ተጀምሯል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE