የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መቀሌ ተያዙ ።

መረጃዎች እንዳመለከቱት ቡድኑ የተጓዘው መቀሌ የተሸሸጉትን በሙስና እና በሽብር ተግባር የተሰማሩ የሕወሃት ቱባ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከትግራይ መስተዳደርና ከፖሊስ ኮሚሽኑ እንዲሁም ከትግራይ ጸረ ሽብር ግብረ ኃይል ጋር ተነጋግሮ የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዞ ወደ መቀሌ እንደበረረ ሲያወቅ በጉዳዩ ጣልቃ የገቡት የመከላከያ ሹማምንት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ጨምሮ ባደረጉት ተልእኮውን የማክሸፍ ስራ ከመሃል ሃገር የሔዱት ፖሊሶች ታስረው አንቶኖቩ ባዶውን እንዲመለስ ተደርጓል።

ተልእኮውን ካከሸፉ በኋላ የተሳሳተ መረጃ በማዘጋጀት በጀርመን ድምጽ ራዲኦ እንዲተላለፍ ያደረጉ ሲሆን የጀርመን ድምጽ ራዲኦ ጽፈው የሰጡትን ሳያጣራ ሳይመረምር በማስተላለፍ ሕዝብን አደናግሯል። ከዚህ በታች ያለው የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘገባ ነው።

የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ የፀረ-ሽብር ግብር ኃይል የሚል መለዮ እና አርማ ያደረጉ ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መቀሌ፤ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣቢያ ተያዙ። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ምንጮች ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ታጣቂዎቹን ያሳፈረዉ አንቶኖቭ አዉሮፕላን መቀሌ ያረፈዉ ዛሬ ጠዋት ነዉ።

መትረየስ ጭምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያ የታጠቁት ሰዎች ከሱዳን አዲስ አበባ ለመጓዝ አልመዉ በስሕተት መቀሌ ማረፋቸዉን ተናግረዋል ተብሏል።ዉስጥ አዋቂ ምንጮቻችን እንደሚሉት የትግራይ መስተዳድር ልዩ ኃይል ታጣቂዎቹን ክብቦ ጉዳዩ እየተጣራ ነዉ።

DW amharic


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE