የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት መቀበል አለበት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

“የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ በፌደራል መንግስቱ እና በአማራ ክልል መንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት መቀበል አለበት” –  ዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር
(ኢ.ፕ.ድ) የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ በፌደራል መንግስቱ እና በአማራ ክልል መንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት መቀበል አለበት ሲሉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ።
የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ በፌደራል መንግስቱ እና በአማራ ክልል መንግስት የተደረገለትን የሰላም ጥሪ በሙሉ እምነት በመቀበል ከአማራ ህዝብ ጋር በሰላም እንዲቀላቀልና ከአካባቢው መስተዳድር አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ፈጣን ሰላማዊ ሽግግር ለማስፈን የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርግ ዶ/ር አብረሀም ጠይቀዋል።
ለአመታት ዋጋ እየከፈለ ባለው የአገር የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በወሰደው አሳፋሪ የጥቃት ትንኰሳና ዝርፊያ መነሻነት የፌደራሉ መንግስት መጠነ ሰፊ ህግ የማስከበር እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን ዶ/ር አብረሀም ተናግረዋል።
በአይነቱና በታሪክም ፍፁም እንግዳ የሆነ የክህደት ተግባር ለአገራቸው አንድነትና ክብር ለአመታት መስዋእትነት ለከፈሉ ህዝቦች ጠላፊው ቡድን ያለውን ንቀት ያሳየበት ነው፤ ያለዑት ዶ/ር አብረሀም፤ በዚህ የለየለት እብደቱም የአገርን ሉአላዊነት አደጋ ላይ የጣሰ በመሆኑ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃዎች በሙሉ እየተወሰደበት ይገኛል ብለዋል።
መንግስት ሰላምና መረጋጋትን በመላው ትግራይ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የህግ ተግባራትን በመደበኛው የህግ አግባብ ለማስፈፀም አዳጋች መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዛሬው እለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጁን ተናግረዋል።
“በአገር ላይ የተቃጣውን የክህደት ተግባር መላው የትግራይ ህዝብ ከመከላከያ ሐይል እና ከመላው የአገራችን ህዞቦች ጋር በጋራ በመቆም በፅናት እንድትመክቱና ይህንን አስከፊ የክህደት ተግባርም በጥብቅ በማውገዝ ከመንግስት ጎን እንትቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፤ ዶ/ር አብረሀም።