በተስፋ ጌታሁንና ፈይሳ ሌሊሳ በወንዶች ነፃነት ጉደታ በሴቶች የቦጎታውን ማራቶን አሸነፉ።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች የቦጎታ ግማሽ ማራቶንን አሸነፉ

******************************************

በኮሎምቢያ ርዕሰ መዲና ቦጎታ በየካሄደው የግምሽ ማራቶን ውድድር በወንድም በሴትም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ ሆኑ፡፡

በውድድሩም በሴቶች የግማሽ ማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያዊቷ ነፃነት ጉዴታ 1ኛ ስትወጣ በወንዶች ውድድር ደግሞ በተስፋ ጌታሁን ቀዳሚ ሆኗል፡፡

አትሌት ነፃነት ርቀቱን በ1፡11፡34 ጊዜ ነው ያጠናቀቀችው፡፡

27 ዓመት እድሜ ያላት አትሌት ነፃነት ጉዴታ በዚህ ዓመት ብቻ በርቀቱ ለሶስተኛ ጊዜ አሸናፊ መሆን እንደቻለች ተነግሯል፡፡

በሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ ኬንያዊቷ ብሪጂድ ኮስጂ ሁለተኛ፤ ኢትዮጵያዊቷ ደጊቱ አዝመራው ደግሞ ተከታዮን ስፍራ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

በተመሳሳይ እርቀት ከፍተኛ ፎክክር በታየበት የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው በተስፋ ጌታሁን በ1፡05፡10 ጊዜ ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ ሆኗል፡፡

በእርቀቱም ሌሊሳ ፈይሳ በ1፡05፡23 ሰዓት 2ኛ፤ ኬንያዊው ዲክሰን ቹምባ 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንስ ማህበር የወርቅ ደረጀ የተሰጠው ይህ የግማሽ ማራቶን ውድድር ለ19ኛ ጊዜ እንደተካሄደ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ IAAF


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE