ህወሓት ወልቃይት ላይ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ ከሽፎበታል!

ትህነግ/ህወሓት ወልቃይት ላይ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ ከሽፎበታል!

ትህነግ/ህወሓት ዛሬ ሀምሌ 22/11-2010 በወልቃይት አዲረመጥ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ ነሸር። ሆኖም የወልቃይት አዲረመጥ ከተማ ሕዝብ ሰፊ የሆነን ተቃውሞ ስላጋጠመው ሰልፉ እንደታሰበ በአደባባይ ሳይካሔድ ቀርቷል። ከ50 በማይበልጡ የትህነግ/ የህወሐት ካድሬዎች በአዳራሽ መወያየታቸው ተገልፆአል። ሰልፉ የከሸፈው የከተማው ሕዝብ አድማ በማድረጉ መሆኑ ታውቋል።

በስብሰባውም “የወልቃይት ሕዝም ለምን እምብይ አለ? ብለው መወያየታቸውም ታውቋል። ለዛሬው ሰልፍ የወልቃይት ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች በሰልፉ እንዲገኙ፣ ካልተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዛቻ የደረሰባቸው ቢሆንም ትህነግ/ህወሓት ባሰበው መንገድ ሰልፍ እንደማይሳተፉ መግለፃቸው ታውቋል።

“ወልቃይት አማራ ነው! ለውጡ እና የለውጥ ሐይሉም እንደግፋለን!” የሚል መፈክር ይዘን መውጣት የምትፈቅዱ ከሆነ ሰልፉን እንቀላቀላለን በማለታቸው ከትህነግ ካድሬዎች ጋር አልተስማሙም።

ሰራተኞቹ “እናንተ በእኛ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። የእኛ ትክክለኛ እና እውነተኛ አቋማችን በማንገልፅበት እና በማይንፀባረቅበት ሰልፍ አንገኝም፣ አንሰለፍምም” በማለት ከሰልፉ ሳይገኙ ቀርተዋል።

የትህነግ/ህወሓት ካድሬዎች “ወልቃይት የትግራይ ነው፣ ጎንደር ያሉት የወልቃይት ኮሚቴዎች አይወክሉንም” የሚል መፈክር አሳትመው ሰልፍ ለመውጣት ቢጥሩም ሕዝቡ የስራ ማቆም አድማ በማድረጉ ሰልፉ ሳይሳካ ቀርቷል። ሰልፉ የከሸፈባቸው የትህነግ ካድሬዎች በአዳራሽ ለመወራረት ተገድደዋል ተብሏል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE