የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ-ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤቴክርስትያን ተፈጽሟል።

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ አስክሬን ወደ ቀብር ቦታው ከመሄዱ በፊት ለአንድ ታላቅ የልማት ጀግና በሚደረግ ሥነ-ሥርዓት ታጅቦ በመስቀል አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎለታል።

በቀብር ስነስርዓቱ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና በርካታ ህዝብ ተገኝተዋል።

ተውኝ አትቀብሩኝ ምን አደረኳችሁ
ሌት ተቀን ሠርቼ ባገለገልኳችሁ
የላቤን ነው እንጂ ጉቦ አልበላሃችሁ
እኔ ውሀ ሢጠማኝ ውስኪ እየጠጣችሁ
ፅሀዮ ሢመታኝ ምቾት ሢጨናችሁ
የኔን መገደል ሤራ እያሤራአችሁ
እኔ ሠራተኛ መች ጠረጠርኳችሁ
ተውኝ አትቅበሩኝ ልኑር በናታችሁ
ግን ለምን 😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ግን ለምን እኔን ገዳችሁኝ
ኢትዮጵያን ላሥፋት ላሥጠራት ባልኩኝ
ሌት ተቀን በርሃ ኑሮየን ባደረኩኝ
ለኢትዮጵያ ሥል ቤቴን በዘጋሁኝ
ግን ለምን ገደላችሁኝ 😭😭😭😭😭😭😭😭
ልጆቸን ትቼ በርሀ የገባሁኝ
ለሽብር አይደለም እኔ እስካወኩኝ
ልጄ ናፍቄህ እንኳን ሥትለኝ
ናፍቆቷን ችየ ቀረሁ ሣላገኝ
ልጀ እንኳን ናፈኩ አባየ ሢለኝ
ናፍቆቱን ይዤ ገደላችሁኝ😭😭
አባቴን 👈
አባቴን ሣልቀብር ቀበራችሁኝ
ልጀ ናፈኩኝ እያለ ሢለኝ
አባቴ እመጣለሁ እያልኩት ጠብቀኝ
አቅመ ደካማ ነው ያውም ሽማግሌ
ምንስ ብሰራ ነው ምን ሆኖ በደሌ
እኔ እስተማውቀው የኔ ጥፋቴ
በነዳዳ ፅሀይ በርሀ መሥራቴ
ለኢትዮጵያ ብየ ትቸ ክብር ቤቴ
ፍረጂኝ ኢትዮያ 😢👇
ፍረጂኝ ኢትዮጵያ አንች ትልቅ ሀገር
ምንስ በድየ ነው ያሠርጁኝ ከአፈር

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ፍትህ ፍትህ

ያም ይሁን ይህ እንግዲህ ወገኔ
አልተመለሥኩም ህጃለሁ እኔ
ገዳየን አቅርቡ ለፍርድ እላለሁ
ልጆቸም ሢያድጉ እንዳይርግሟችሁ
ገዳየን አቅርቡ ለንፁህ ብላችሁ
ኢትዮጵያ ሀገሬ እንዳታዝንባችሁ
እኔሥ ሂጃለሁ ዳግም ላላያችሁ
ገዳይ ወዮላችሁ
ገዳይ ወዮላችሁ
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ፍትህህህህህህህ

ኢንጂነሩ ባለፈው ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም በመኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኛታቸው ይታወሳል።

መስከረም 3/1957 ዓ.ም በጎንደር ማክሰኝት የተወለዱት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ነበሩ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE