በወለጋ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎች በታጣቂዎች መፈፀማቸው ተሰማ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በታጠቁ ሀይሎች ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ፡፡ ጥቃቱ በአካባቢው በሚኖሩ አርሶ አደሮች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደነበረም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። በወረዳዋ ከመሰከረም ወር ጀምሮ ተመሳሳይ ጥቃቶች ሲደርሱ እንደነበርም ነው ነዋሪዎቹ ያመለከቱት። የአሙሩ ወረዳ ፖሊስ በበኩሉ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጦ ነገር ግን ማንነትን መሰረት ያደረገ አይደለም ሲል ክሱን አስተባብሏል።DW